Ibn Zura

ለበደለችም ነፍስ ሁሉ በምድር ላይ ያለው ሁሉ ቢኖራት ኖሮ በእርግጥ በተበዠችበት ነበር፡ (ቁርአን 10:54)

እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ። (የዮሐንስ ወንጌል 1:29)

ይህ የኢብን ዙራ ድህረ-ገጽ የክርስቲያንና የሙስሊም ውይይት ነው፡፡ የማንንም እምነት ለማጥቃትም ሆነ ለማንቋሸሽ ሳይሆን፡ ይልቁንም ሰዎች መልስን ለማግኘት በሚያደርጉት ጥረት ለመርዳት የሚያስችል ነው። ክርስቲያኖች ባሉበት አካባቢ የሚኖሩ ሙስሊሞች፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮችን ሊረዱና የኑሮአቸውን ዘይቤ ለማወቅ ይፈልጋሉ። የክርስትናን ባህርይ ለመረዳትም ያሳስባቸዋል። ሙስሊም እንደ መሆንህ መጠን የራስህን ሃይማኖት መረጃ መፈለግህ አይቀርም። ሰው ሁሉ ሊያቀርባቸው የሚችላቸውን ጥያቄዎች፡ ለምሳሌ፡ እንዴት ነው መጽደቅ የምችለው? ኢየሱስ ማነው? በቁርኣን ዒሳ የተባለውና በመጽሓፍ ቅዱስ ኢየሱስ የተባለው ያው አንድ ናቸው እንዴ? እርሱ በእርግጥ ነቢይ ብቻ ነበር እንዴ?

ጥያቄዎች? እባኮህ እኛ ያግኙን፡